አንድ ከኤች አይ ቪ ጋር የሚኖር ሰው በምርመራ ሊገኝ የማይችል ኤች.አይ.ቪ. በደሙ ውስጥ ያለ ሰው (undetectable) በሚሆንበት ጊዜ ፣ ሰውየው ጤናማ ከመሆኑም በተጨማሪም ኤች.አይ.ቪን ወደ ሌላ ሰው ሊያስተላልፍ እንደማይችል ሳይንስ አረጋግጧል። ወይም፦ በምርመራ ሊገኝ የማይችል ኤች.አይ.ቪ. በደሙ ውስጥ ያለ ሰው (undetectable) = ሊተላለፍ የማይችል(Untransmittable) (U = U)።
ይህ በኤች.አይ.ቪ. ታሪክ ውስጥ ድንቅ እድገት ነው። ይህ ማለት በምርመራ ሊገኝ የማይችል ኤች.አይ.ቪ. በደማቸው ውስጥ ያለ (undetectable) ሰዎች ቫይረሱን ወደ ወሲብ አጋሮቻቸው እንዳያሰተላልፉ ሊያስፈራቸው የሚችል ምክንያት የለም። ከኤች.አይ.ቪ. ጋር የሚኖሩ ሰዎች ጤናማ ሆነው ለመቆየት በየቀኑ የሚወስዷቸውን መድሃኒቶች በመውሰዳቸው ብቻ ኤች.አይ.ቪ.ን ለመግታት የመፍትሄ አካል ናቸው።
www.uequalsu.org ን ይመልከቱ። (ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ መረጃ አገናኝ/Link )