ኤች.አይ.ቪ (HIV) ሂዩማን ኢሚዩነውዲፊሸንሲ ቫይረስ ፤ለማለት ነው። ኤች.አይ.ቪ የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓት አቅም በማዳከም ሰውነትዎ ጤናማ ሆኖ ለመቆየት እንዳይችል በጣም ከባድ ተጽኖ ያሳድርበታል። ኤች.አይ.ቪ ቀስባቀስ ወደ አኳየርድ ኢሚዩነውዲፊሸንሲ ሲይንደሮም (ኤድስ/AIDS ሊያመራ ይችላል።
ደግነቱ የሰውነታችን በሽታ የመከላከል ስርዓት ጠንካራ እንዲሆን ለማድረግ ውጤታማ የሆኑ ህክምናዎች አሉ። በአሁን ሰዓት የኤች.አይ.ቪ. መድሃኒቶችን በጊዜ በመጀመር እና በአግባቡ በመከታተል ኤች.አይ.ቪን መቆጣተር ይቻላል። ብዙ መሻሻሎች ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን በመደረግም ላይ ናቸው። ዛሬ ኤች.አይ.ቪ. በደማቸው ውስጥ ያለባቸው (ኤች.አይ.ቪ. ፖዘቲቭ) ሰዎች መድሃኒታቸውን በአግባቡ ተከታትለው መውሰድ ከቀጠሉ ልክ ኤች.አይ.ቪ በደማቸው ውስጥ የሌለባቸው ሰዎች መኖር እንደሚችሉት ያክል እድሜ መቆየት ይችላሉ።
ይህን የ ከኤድስ የበለጠ (Greater Than AIDS) የአንድ ደቂቃ ቪዲዮ ይመልከቱ። (ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ መረጃ አገናኝ/Link )