መሳሳም፣ ጋራዊ ማስተርቤሽን (mutual masturbation)፣እና መደባበስ(frottage) ለኤች.አይ.ቪ አደጋ አያጋልጡም። በአፍ የሚፈጸም ወሲባዊ ግንኙነት፣ ፍንጢጣን በምላስ መዳበስ (rimming)፣ኮንዶም ተጠቅሞ ማጥቃት (topping with a condom) እና ኮንዶም ተጠቅሞ መጠቃት (bottoming with a condom) በኤች.አይ.ቪ. የመያዝ አደጋቸው በጣም ዝቅተኛ ነው። ኮንዶም ሳይጠቀሙ ማጥቃት (topping without a condom) መካከለኛ በኤች. አይ. ቪ. የመያዝ አደጋ ሲኖረው ኮንዶም ሳይጠቀሙ መጠቃት (bottoming without a condom) ከፍተኛ በኤች.አይ.ቪ. የመያዝ አደጋ አለው።
ይሄ የሚመለከተው ኤች.አይ.ቪ.ን ብቻ ነው ፤ እንደ ሲፊልስ፣ ጨብጥ ፣ ክላሚዲያ ፣ ወይም ሄፓታይተስ መሳሰሉ ሌሎች ኤስ.ቲ.ዲዎችን/STDs (በግብረስጋ ግንኙነት ለሚተላለፉ ያባላዘር በሽታዎችን) አይመለከትም።