የዚህ ጥያቄ መልስ ውስብስብ ነው። ለኣንዳንድ ሰዎች በተለይም ኤል.ጅ.ቢ.ቲ. (LGBT) መሆን ሕገወጥ በሆነበት ወይም በአገልግሎት ሰጭዎችና እና በበሽተኞች መካከል ሊኖር የሚገባው ግላዊነት (privacy) ህጋዊ ዋስትና በማይሰጥባቸው ሀገሮች ውስጥ ወደ ህክምና አገልግሎት ሰጭዎች ለመምጣት ደህንነት ላይሰማቸው ይችላል።
ይሁን እንጂ የህክምና አገልግሎት ሰጭዎችቻችንን ልናምናቸው የምንችል ከሆነ በተሻለ ሁኔታ ሊያስተናግዱን ይችላሉ። ስለ ፆታ ማንነትዎ (gender identity)፣ ስለ ወሲባዊ ዝንባሌዎ(sexual orientation) እና ስለሚፈጽሙት የወሲብ አይነት ቢነግሯቸው እርሰዎ ጤናማ ሆነው እንዲቆዩ የሚያስፈለገዎትን ትክክለኛ ምርመራ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል።
ያስታውሱ ከዶክተርዎ ጋር ጤናማ ብቻ ሳይሆን ከኀፍረትም ነፃ የሆነ ተሞክሮ ሊኖርዎት ይገባል። አንድ ዶክተር ወሲባዊ ዝንባሌዎ (sexual orientation )፣ የፆታ ማንነትዎ (gender identity) ወይም የሚፈጽሙት የወሲብ አይነት የተሳሳተ መሆኑን ሊነግርዎ ቢሞክር፣በጉብኝዎ ወቅት ስለ መድሃኒት ብቻ ማውራት እንደሚፈልጉ በትህትና ይንገሯቸው።
ይህን የ ከኤድስ የበለጠ (Greater Than AIDS) የአንድ ደቂቃ ቪዲዮ ይመልከቱ። (ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ መረጃ አገናኝ/Link )