የዚህ ጥያቄ መልስ እርስዎ በሚፈጽሙት የግብረ ሥጋ ግንኙነት አይነት ይወሰናል። በአብዛኛው ዶክተሩ የኤች.አይ.ቪ. ምርመራ፣ የቂጥኝ የደም ምርመራ እና የሽንት ምርመራ ለኤስ.ቲ.ዲዎች (በግብረስጋ ግንኙነት ለሚተላለፉ ያባላዘር በሽታዎች) ያደርጋሉ። በአፍ ወሲብ ከፈፀሙ ሃኪምዎ በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ያባለዘር በሽታዎች መኖር አለመኖራቸውን ለማጣራት ከአፍዎ ናሙና መውሰዳቸውን ማረጋገጥ አለብዎት። እንዲሁም ተጠቂ (bottom oriented) ከሆኑ ዶክተርዎ በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ያባለዘር በሽታዎች መኖር አለመኖራቸውን ለማጣራት ከፊንጥጣዎ ናሙና መውሰዳቸውን ማረጋገጥ አለብዎት።
ቢያንስ አንድ ጊዜ የሄፐታይተስ ቢ እንዲሁም የሄፓታይተስ ሲ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው ፤ በተለይም ኤች.አይ.ቪ. ቫይረስ ካለብዎ።
ይህን የ ከኤድስ የበለጠ (Greater Than AIDS) የአንድ ደቂቃ ቪዲዮ ይመልከቱ። (ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ መረጃ አገናኝ/Link )