በምርመራ ሊገኝ የማይችል ኤች.አይ.ቪ. በደሙ ውስጥ ያለ ሰው (undetectable) ማለት አንድ ሰው የኤች.አይ.ቪ. ቫይረስ በደሙ ውስጥ ያለ ቢሆንና ህክምናውን በትክክል ቢከታተል በህክምናው ጫና ምክንያት ቫይረሱ በሰውነቱ ወስጥ ይደበቃል። በዚህም የተነሳ ምርመራዎች ቫይረሱን በደም ናሙና ውስጥ ሊያገኙት አይችሉም።
አንድ ከኤች አይ ቪ ጋር የሚኖር ሰው በምርመራ ሊገኝ የማይችል ኤች.አይ.ቪ. በደሙ ውስጥ ያለ ሰው (undetectable) በሚሆንበት ጊዜ ፣ ሰውየው ጤናማ ከመሆኑም በተጨማሪም ኤች.አይ.ቪን ወደ ሌላ ሰው ሊያስተላልፍ እንደማይችል ሳይንስ አረጋግጧል። ወይም፦ በምርመራ ሊገኝ የማይችል ኤች.አይ.ቪ. በደሙ ውስጥ ያለ ሰው (undetectable) = ሊተላለፍ የማይችል(Untransmittable) (U = U)።
አንድ ሰው የታዘዘለትን መድሃኒት በትክክል እስከወሰደ ድረስ በምርመራ ሊገኝ የማይችል ኤች.አይ.ቪ. በደሙ ውስጥ ያለ ሰው (undetectable) ሆኖ ይቆያል::
በምርመራ ሊገኝ የማይችል ኤች.አይ.ቪ. በደሙ ውስጥ ያለ ሰው (undetectable) ሆኗል ማለት ከኤች.አይ.ቪ. ተፈውሷል ማለት አይደለም ፤ ነገር ግን አንድ ውጤታማ የኤች.አይ.ቪ. መከላከያ አማራጭ ነው።
ከኤች.አይ.ቪ. ጋር ከሚኖሩ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ በምርመራ ሊገኝ የማይችል የቫይረስ-ጭነት (viral load) የለባቸው። እነዚህ ሰወች እንደ ኮንዶምና ፕሪፕ (PrEP) ያሉ የኤች.አይ.ቪ. መከላከያ አማራጮችን በመምረጥና በመጠቀም ደህንነቱ የተጠበቀ የግብረስጋ ግንኙነት እንዲኖራቸው ማድረግ ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ TheBody ወይም www.UequalsU.org ን ይመልከቱ። (ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ መረጃ አገናኝ/Link ).